XtGem Forum catalog
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

–––•(♥-•(☀)•-♥)•–––
ለልጆቻችን ያለብን ኻላፊነቶች
–––•(♥-•(☀)•-♥)•–––


999352 552619304802201 1239176316 n 1

ክቡራን ወላጆች ልጆቻችን ከኻያሉ አሏህ የተሰጡን ጸጋዎች ናቸው። እነዚህን የዓይኖቻችነን ማረፊያዎች ፈጣሪያችን ሲሰጠን ግን ከተወሰኑ ሃላፊነቶችቶችና ግዴታዎች ጋር መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ይህ የኢስላም ሃይማኖት ሲሆን ቀና የሆነ ብቸኛ መንገድ ነው። እናም የአብራካችን ክፋዮች የሆኑ ልጆቻችነን በተገቢው መንገድ በማነፅ የነገውን ኢስላማዊ ትውልድ እንዲቀላቀሉና የአሏህ ባሮች እንዲሆኑ በትጋት መስራት ከእኛ ከወላጆች ይጠበቃል። ይህን ጉዳይ በማስመልከት ከሁሉም ነገር በላይ ተወዳጅ የሆኑት መልእክተኛ( ሰ.ዐ.ወ) ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:-

«ሁላችሁም እረኞች ናችሁ። ከምትጠብቁት ነገር ትጠየቃላችሁ። ባል የቤተሰቡ ጠባቂ ነው። ስለሆነም በቤተሰቡ ጉዳይ ይጠየቃል። ሚስት የባሏን ቤት ጠባቂ ናት። ስለሆነም የባሏን ቤት በተመለከተ ተጠያቂ ናት።»


ወላጆች ልጆቻቸውን አሏህን ለማስደሰት በማሰብ እርሱ በሚፈልገው መንገድ ካሳደጉ መልካም ሦራን.... ሃያሉ አሏህ በፍርዱ ቀን ምንዳቸውን እጥፍ ድርብ በማድረግ ይከፍላቸዋል። በልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ከእነርሱ በኋላ በሚፈጠሩትና እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ቀናውን ጎዳና በሚከተሉት ዝርዮቻቸው ጭምር ምንዳን ያገኛሉ። ይህ ታላቅ እድል ነው። ከዚህ በተቃራኒው ልጆቻቸው ዝንባሌያቸውን እንዲከተሉና መረን የለቀቁ እንዲሆኑ በማድረግ ያሳደጉም ተቃራኒውን ያገኛሉ። ኃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል:-


-<({አል-ቁርአን 55:60})>-

«የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን?»

-<({አል-ቁርአን 18:46})>-

«ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው። መልካሞቹም ቀሪዎች ሦራዎች እጌታህ ዘንድ በምንዳ በተስፋም በላጮች ናቸው።»

–––•(♥-•(☀)•-♥)•–––
ሴት ልጆች በኢስላም ያላቸው ሦፍራ
–––•(♥-•(☀)•-♥)•–––


168830 10152795434405608 237932136 a

የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-

«አንድ ሙስሊም ሰው ሁለት ሴት ልጆች ቢኖሩትና ለእነርሱ ጥሩ በሆነ ተርቢያ ካሳደጋቸው ጀነት ለመግባት ሰበብ ይሆኑለታል።»

እንግዲህ ማንም ቅን ልብ ያለው ሰው ይህንን የነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ክብደት ሊሰጥጠውና ለነገው ዓለም ሕይወት መድህን ያስገኝለት ዘንድ በሚገባ አኴኋን ሴት ልጆቹን ሊያሳድግ ግድ ይለዋል።

ኃያሉ አሏህ የሰውን ልጅ ሲፈጥር ወንድና ሴት አድርጎና እንደ ማንኛውም ፍጡር የሁለትዮሽን መንገድ ተከትሎ ነው። ይህም በቀጣዩ የቁርአን አንቀፅ ተገልፇል።


-<({አል-ቁርአን 30:30})>-

«ወደ እውነት ተዝንባይ ሆነህ ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ። የአሏህን ፍጥረት ያችን አሏህ ሰዎችን በርሷ ላይ የተፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት። የአሏህን ፍጥነት መለወጥ የለም። ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው። ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።»

በሌላ በኩል ደግሞ አንዱ ጾታ ሌላውን መፈለጉና የዚያ አይነት የተቃራኒ ፆታ ፍለጋ አዝማሚያዎች በተፈጥሮ የተቀመጡ የኃያሉ አሏህ ሦራዎች መሆናቸው በቁርአን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል:-

--<({አል-ቁርአን 3:14})>--

«ከሴቶች ፣ ከወንዶች ልጆችም ፣ ከወርቅና ከብር ከተከማቹ ገንዘቦችም ፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም ፣ ከግመል ፣ ከከብትና ከፍየልም ፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ።»

ይህ እርስ በርስ የመፈላለግ ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ታዲያ በቁጥጥር ሥር ካልዋለና በመንፈሳዊ እንዲሁም በኢስላም የሥነ-ምግባር አስተምህሮቶች ካልተለጎመ የሰውን ልጅ አይወድቁ አወዳደቅ ይጥለዋል። የአሏህ ነብይ (ሱ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-

«ከእኔ በኋላ ከሴቶች የበለጠን ፈተናን በወንዶች ላይ አልተውኩም። የእስራኤል ልጆች እንዲወድሙ ምክኒያት የሆኗቸው ሴቶች ነበሩ።»

64408 536080006442719 178953258 n 1

ውድ እህቴ አንቺ የመጭው ኢስላማዊ ትውልድ ተረካቢ የሆነ (የሆነች) ህፃን የሚፈሩበት ንፁህ ማህጸን ይዘሻል። አሏህ ባንቺ ማህጸን ውስጥ ኢስላምን የሚያልቁና የእርሱንም ክብር ከፍ የሚያደርጉ ልጆች ይጸነሱበት ዘንድ ፈቃዱ እንዲሆን እነሆ ራስሺን በማንፃት አመቻቺ። ይህ ማንፃት ማለት ደግሞ ሌላ ሳይሆን እርሱን በመፍራት ወደ ርሱ መቃረብ ነው።


Websites:
http://youth-mission.mobie.in

http://youth-mission.blogspot.com

ምንጭ:
ሼይኽ አብዱል ኻሊቅ አሸሲፍ
©ትርጉምና ጥንቅር: አህመድ ሁሴን

1391

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ